Poetry at Fendika - Frezer Admasu
Embedded in Tamrat Gezahegne’s installation at Fendika is a poem in Amharic, written by poet Frezer Admasu, a frequent visitor of Fendika Cultural Center. With his permission, we share his poem here in Amharic and English (in this order), as well as his bilingual reflection on Fendika as a creative home. You can also listen to the poem read this poem in the video included here.
ይህ ግጥም…!
በሁሉም ጊዜ የሚኖር
የትም ስፍራው የሆነ
ሁኔታ የማይገድበው
በፍጥረት መንፈስ ያደረ
አንድ ሐሳብ ነበረ…
የመሬትን ስበት አቁሞ
ሰማየ ሰማያት የሚያደርስ
መልኩ ውኃ የሆነ
አካሉም ልክ እንደ ንፋስ
ይህ ግጥም ጠበል ጠዲቅ ነው
ለዘርዐ ሰብ የሚቋደስ::
ይህ ግጥም
ምንም ነው
አንዳች ነገር የሆነ
በጸጥታው የሚጮህ
በሐሳብ ቃል የተካነ::
ይህ ግጥም
ፆታ አልባ ነው
ተሰይሞም ያላወቀ
ሀገሩ የትም የሆነ
አለማወቁን ያወቀ::
ያልተጀመረ ሐሳብ ነው
ለማለቅ ያልተፈጠረ
በሞት ውስጥ ህይወት የሆነ
በወል ሕግ የተቋጠረ::
ይህ ግጥም
ወይን ጠጅ ነው
በሰው ራስ የተጠመቀ
ገጣሚ ኖሮት የማያውቅ
ከምናብ ስር የፈለቀ::
ይህ ግጥም
እርግማን ነው
በእርኩሰት ላይ የተነሣ
ኃጢአትን በፍቅር ሰቅሎ
የጽድቅ ማዕበል ያስነሣ::
ይህ ግጥም
እንዲህ አይደለም
እንደዚያም ሆኖ አያውቅም
ውጤቱ ምክንያቱ ነው
ውልደቱ ለሞቱ እሚቆም::
ይህ ግጥም
ፊደል የለውም
ከቃልም አልተፈጠረ
መሆንን ካለመሆን ጋር
አስማምቶ በሕግ ያኖረ::
ይህ ግጥም
ቤት የለውም
ተፈጥሮው ዱር አዳሪ ነው
ያለመኖሩ መገለጥ
ለዝንተ ዓለም የሚያኖረው::
ይህ ግጥም
ቋንቋ አልባ ነው
ሁሉንም ያነጋግራል
መነሻ ኖሮት አያውቅም
የትም ግን መድረስ ይችላል::
በሰው እጅ ስላልተጻፈ
ይህ ግጥም አይነበብም
ለነፍሳት ሁሉ ይሰማል
ድምፅ ኖሮት ግን አያውቅም::
ይህ ግጥም
ሰማያዊ ነው
ቀለመ ቀስተ ደመና
ቅርንጫፉም ቁልቁል ነው
ስሩ ከላይ ነው እና፡፡
ይህ ግጥም የተፀነሰው
ከሐሳብ ማኅፀን ውጪ
ከምንም እራስ ነው እና
ልጅ መሆን አያውቅበትም
አይነካካውም እርጅና::
እና…
በሁሉም ጊዜ የሚኖር
የትም ስፍራው የሆነ
ሁኔታ የማይገድበው
በፍጥረት መንፈስ ያደረ
አንድ ሐሳብ ነበረ…
ይህ ግጥም…!
This Poem
A matter of eternity,
An entity.
Omni-present everywhere
unconquered by intrusion
enshrined, in the spirit of all creatures
Once there was an idea.
It captivates gravity
to soar us yonder into the skies.
It has a water-complexion
its body, wind-like.
This poem is the holy water and bread
To be delivered to mankind …
This poem is a non-entity
and yet so great a being
shouts by power of silence
ordained by the word of thought.
This poem is genderless
never in nomenclature
its address is everywhere
and knows, that it knows not!
It is an idea not yet begun
created not to be ended
its life is within death
with common laws it is at ease.
This poem is a “wine-tej”
fermented by human mind
it never had a poet or writer
abruptly it springs, underneath imagination.
This poem is a condemnation
that rose against all evils
with its love, its crucified sins
drives ebbs and waves of bliss.
This poem is neither here or there
hitherto it exists
its cause is its effect
and its birth stands for its own death.
ከፈንድቃ ጋር ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት በልዩ ኪነጥበባዊ ህብረት ከህይወት ጋር ስንታደም ኖረናል፡፡ፈንድቃ ለእኔ የመነቃቂያ እና የተመስጦ ስፍራዬ ነው፡፡በሀሳብ እና በተግባር ከምመስላቸው ነፍሶች ጋር ያለ ብሔር߹ፆታ߹እና ሀይባማኖት በፍጹም ምናባዊ ሰውነት ብቻ የምዋሀድበት ዐውድ ነው፡፡
ፈንድቃ የመሆን ወይም ያለመሆን ስፍራ ነው፡፡
ፈንድቃ ውሥጥ ሙዚቃ߹ግጥም እና ስዕል በልዩ ህልውና ተጣጥመው እናገኛቸዋለን፡፡እነርሱም እኛን ያገኙናል፡፡
በፈንድቃ ሰማይ
ኮከብ ሆኖ በርቶ
ደምቆ ለመገኘት
ከፍ ዝቅ የሌለው
በቂ ነው ሰውነት፡፡
ፈንድቃ ነበር߹አለ ይኖራልም!
For the last two decades I and Fendika were harmonized with life through different creative art unification. For me Fendika is a time and space where my soul gets motivated and meditated.
I get harmonized with varieties of beings in resemblance with my action and imagination without a barrier and influence of race, religion and gender.
Fendika is venue of to be or not to be.
Music, poetry and visual art reside at Fendika in monastic state of harmonization, in such a way we meet them there and the reverse is true.
As a star…
To gleam and twinkle
On the dark black sky of “Fendika”
With a none state of topping and/or bottoming
Being human is the coding.
FENDIKA, is an “is” a “was” and a “will” as well!